የባል ና ሚስት ቀልዶች – Amharic jokes

አማርኛ ቀልዶች amharic jokes

ባል ና ሚስት

1. ሚስት:- ጡት ማስያዣ መግዛት ስለምፈልግ ትንሽ
ገንዘብ ስጠኝ?!
.
.
.
ባል:- እንዴ ምኑን ልታስይዥበት ነው?!
.
.
.
ሚስት:-ምነው አንተስ ፓንት ታደርግ የለም እንዴ?!

2. ባልና ሚስት እራት እየበሉ በጨዋታ መሃል
ሚስት:- ፍቅሬ እስቲ ሳትደብቅ ንገረኝ እኔን ከማግባትህ
በፊት ስንት የሴት ፍቅረኞች ነበሩክ?
ባል :- ለ5 ደቂቃ ዝም አለ።
ሚስት:- ከ5 ደቂቃ በኃላ ፍቅር ጥያቄዬን መልስልኝ
እንጂ ብላ ተቆጣች?
ባል:- ዝም ጭጭ ።
ሚስት:- ድጋሚ ከ10 ደቂቃ በኃላ እንዴ ምናባክ ሆነክ
ነዉ አትናገርም እንዴ ብላ ስትጮህ?
ባል:- ጮክ ብሎ
.
.
.
.
እስቲ በፈጠረሽ ዝም በይ ልቁጠርበት።

3. ሚስት( ትደውልና) የማትረባ! ደደብ! የት አባክ ነው
ያለከው?
-ባል፦ ፒያሳ ነኝ!
-ሚስት፦ እዛ ምን ትሰራለሀ?!
-ባል፦አንዴ ትዝ ካለሽ የሆነ ወርቅ ቤት አልጎበኘንም?
-ሚስት፦ አስታወስኩት ውዴ
ባል፦ የወርቅ ሀብል አይተሽ ወደድኩት ስትይ ገንዘብ ሳገኝ
እገዛልሻለው አላልኩም?
ሚስት፦አዎ የኔ ፍቅር.
ባል፦ ወርቅ ቤቱን አወቅሽው?
ሚስት፦አዎ ወለላዬ
ባል፦ከእሱ አጠገብ ያለው ግሮሰሪ ነኝ

4. ሚስት አምሽታ ወደቤት እየገባች ነው …
ወድያው የመኝታ ቤቷን ከፍታ ስትገባ
አልጋዋ ላይ ሁለት የተኙ ሰዎችን
ትመለከታለች፤ አራት እግሮች ከብርድ ልብሱ
ስር ወተው ይታያሉ
ከዝያም ወድያውኑ አጠገቧ ያለውን ዱላ አንስታ
ከብርድ ልብሱ ውስጥ ያሉትን ሁለቱን ሰዎች
ባላት ኃይል መደብደብ ትጀምራለች ..ወድያው
መደብደቡን ታቆምና ወደ ሳሎን ቤት ስትሄድ
ባሏ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ጋዜጣ ያነብ ነበር
ከዝያም ባልየው ” hi darling…ቤተሰቦችሽ
መተዋሉ
የኛ መኝታ ቤት ተኝተዋል ሰላም አልሻቸው ..?
ሲላት ሚስት በድንጋጤ እራሷን ስታ ወደቀች ::
“የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል አሉ”

5. ባል ጣዕረ-ሞት ይዞት እያጣጣረ ሳለ ሚስቱን ያስጠራና
“እንግዲህ እኔ መሞቴ ነው፤ አንቺ ግን ያለ ባል መቅረት
የለብሽም፤ እንዲያውም ያንን ኩራባቸውን አግቢ”
ይላታል። በዚህ አባባል የተናደደችው ሚስት “አንተን
ይማርልኝ እንጂ እኔ አሁን ስለ ባል አላስብም! ደግሞ
ባገባስ እንዴት ያንተን ዋነኛ ጠላት ኩራባቸውን አግቢ
ትለኛለህ?” ስትል ትጠይቀዋለች። በዚህ ጊዜ ጣር የያዘው
ባል እያቃሰተ መለስ ብሎ “አንቺ ደሞ አይገባሽም እንዴ?
ጠላቴ መሆኑንማ መች አጣሁት? ልክ እንደ እኔ
አንገብግበሽ እንድትገድይልኝ ነው እንጂ! አላት ይባላል።
ኑዛዜ ይልሃል ይህ ነው! ከእንዲህ አይነቱ ኑዛዜ
ይሰውራችሁ ይሰውረን አሜን አሜን በሉ።

Share share share please!!!
ከተመቻቹ ሼር ማድረግ አትርሱ!!

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s